Mols.gov.et

ስምምነቱ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በሩሲያ ልዪ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚጠቀሙበትን ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተገለፀ

August 12, 2025
ስምምነቱ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በሩሲያ ልዪ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚጠቀሙበትን ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተገለፀ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር “አላቡጋ” (“Alabuga”) ከተሰኘው የሩሲያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ጋር መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች “አላቡጋ” በተሰኘው ትልቁ የሩሲያ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ መብት፣ ደህንነታቸውና ተጠቃሚነታቸው በተረጋገጠ አግባብ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑበትንና ዘመኑን የዋጀ የክህሎት ስልጠና የሚያገኙበትን ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገልፀዋል። ይህም ዓለም አቀፍ የሥራ ገበያው ላይ ያሉ ዕድሎችን አሟጦ ለመጠቀም የጀመርናቸውን ጥረቶችን የሚያጠናክር ነው ብለዋል። በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በእውቀት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር መስኩ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የገለፁት ክብርት ሚኒስትር ስምምነቱ በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር የሚያስችልና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ስትራቴጂያዊ አጋርነትን የሚፈጥር እንደሆነም አመላክተዋል። ስምምነቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) እና የአላቡጋ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዓለም አቀፍ ትብብር ኃላፊ ኮንስታንቲን ትሪፎኖቭ ናቸው የፈረሙት :: ነሐሴ 3/2017 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር 🌐 Official Website: mols.gov.et 📘 Facebook: facebook.com/MolsFDRE 📣 Telegram: t.me/fdre_mols 🎵 TikTok: tiktok.com/@mols_official 🐦 Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
en_USEN
Scroll to Top