Mols.gov.et

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር እየተሳተፈች ነው

September 11, 2024
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር እየተሳተፈች ነው 47ኛው የዓለም የክህሎት ውድድር በፈረንሣይ ሊዮን በሚካሄድ ላይ ሲሆን ኢትዮጵያ በመድረኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች፡፡ የዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት ኢትዮጵያን 88ኛው አባል አድርጎ የተቀበላት ባለፈው ዓመት ሲሆን በውድድሩ በሦስት (ICT and Networking, CNC Machine, Furniture Making )የሙያ መስኮች ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እየተካፈሉ ይገኛል፡፡ በመድረኩ በ60 የሙያ መስኮች ከ70 አገራት የወጣጡ 1 ሺህ 400 ወጣቶች እየተወዳደሩ ይገኛል። የቴከኒክና ሙያ ስልጠና ለግላዊም ሆነ ሀገራዊ ልማት ያለውን ፋይዳ ማስተዋወቅና ወጣቶች ወደ መስኩ እንዲቀላቀሉ ማነሳሳት፣ ሀገራት የሥራ ገበያውን ፍላጎት በሚመልስ መልኩ ስርዓቱን ተግባራዊ እንዲያደርጉ እና በትምህርትና ስልጠናና በኢንዱስትሪው መካከለ ትብብር እንዲጎለብት ማበረታታት እንዲሁም ሀገራት በዘርፉ ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ እንዲለዋወጡ ማድረግ የውድድሩ ዋና ዋና ዓላማዎች ናቸው። ኢትዮጵያ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራች ሲሆን የክህሎት ልማት ዘርፉ አካባቢያዊና ሀገራዊውን ብቻ ሳይሆን የዓለም የሥራ ገበያው ይዞ የሚመጣውን እድል መጠቀም እንዲቻል ታሳቢ ያደረገ ነው።
en_USEN
Scroll to Top