በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በተጠሪ ተቋማት የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች የደረሱበትን ደረጃ የሚገመግም የውይይት መድረክ ተካሄደ ።
የሪፎርም ቡድኑ አብይና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ባካሄዱት ውይይት በሚኒስቴር መ/ቤቱና በተጠሪ ተቋማት ከአሰራርና አደረጃጀት አንፃር ያሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ነባራዊ ትንተና መሰራቱ ተገልጿል ።
በሥራ ላይ ያሉና መሻሻል የሚገባቸው ፖሊሲዎችን ፣ አዋጆችን ደንብና መመሪያዎችን የመለየት ሥራ መሰራቱም በመድረኩ ተጠቁሟል ።
ምቹ የሥራ ሁኔታን ከመፍጠር አንፃር የህፃናት ማቆያ ፣ የካፍቴሪያ፣የሸማቾች ህብረት ሥራና መሰል አገልግሎቶችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም በመድረኩ ተመልክቷል ።
አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ የማድረግ ሥራ ከሁሉም ቅድሚያ እንደተሰጠው የተገለፀ ሲሆን የአገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ የISO 9001፡ 2015 የጥራት ደረጃን የመተግበር ሒደት በሚኒስቴር መ/ቤቱና ተጠሪ ተቋማት እየተከናወነ እንደሚገኝም ተብራርቷል ።