Mols.gov.et

5ኛው የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጠናዊ የፍልሰት ጉዳዮች የሚኒስትሮች ፎረም …

February 26, 2024
5ኛው የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጠናዊ የፍልሰት ጉዳዮች የሚኒስትሮች ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡ በቀጠናው የሠራተኛ ፍልሰት ጉዳይ የሚመሩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሚሳተፉበት ይህ 5ኛው የሚኒስትሮች ፎረም፤ የመደበኛ ፍልሰት ትሩፋቶች ለወጣቶች የሥራ ዕድል፣ ለክህሎት ልማት እና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ(harnessing the power of regular migration pathways for youth employment, skills development and green economy) በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡ ለቀጣይ አራት ቀናት የሚቆየው ይህ ፎረም በመጀመሪያው ቀኑ በቀጠናው ሀገራት የተከናወኑ ተግባራት እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ተቀምረው ለሚኒስትሮች የሚቀርቡበት የቴክኒካል ቡድን ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ በሊቀመርነት በምትመራው በዚህ ፎረም መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ፤ ይህ የቀጠናው ሀገራት ትብብር በቀጠናው የፍልሰት አስተዳደር የተሳለጠ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል፡፡ ፎረሙ በቀጠናው ነጻ የሰዎች ዝውውር እንዲኖር ለማስቻል፣ በዘርፉ የሚሰሩ ሥራዎች ውጤታማ ለማድረግ፣ ልምድ ለመለዋወጥ፣የስደተኞች መብት ለመጠበቅ ክፍተቶቻችንን ለመለየት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አመልክተዋል፡፡ በመርሃ-ግብሩ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ የቀጣናው አባል ሀገራት፣ የአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስትታት /ኢጋድ/ እና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛል።
en_USEN
Scroll to Top