Mols.gov.et

100,000 የውጭ ሃገር የሥራ ዕድሎች በኢትዮጲያ የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) !

October 6, 2023
100,000 የውጭ ሃገር የሥራ ዕድሎች በኢትዮጲያ የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) ! ለኢትዮጲያ ስኬት ሁሌም እንጥራለን ! በጥረታችን ስኬትም እንበረታታለን! ያለማቋረጥም እንተጋለን! ባለፉት አራት ወራቶች በሥራና ክህሎት ሚኒስትር የውጪ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት ከመቶ ሺህ (100,000) በላይ ዜጎችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ፣ አውሮፓ እና የተለያዩ ሃገራት የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ከሰው ንክኪ ነፃ ሆኖ በቴክኖሎጂ በመታገዝ በዲጂታል ምዝገባ፣ የዜጎቻችንን ደህንነት እና ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም የሚያስጠብቅ እንዲሁም ብልሹ አሰራርን መቀነስ በሚያስችል ቴክኖሎጂ አማካኝነት ዜጎች መሰማራት መቻላቸው የስኬት ጉዞ የመጀመሪያ ምዕራፍ ነው። በተቻለ መጠን ለሁሉም ዜጋ ተደራሽነትን ያረጋገጠ፣ የዜጎችን እንግልት የሚቀንስ፣ በሂደትም የሚያስቀር በውስጥ አቅም ለምቶ ተግባራዊ በተደረገው ቴክኖሎጂ በተቀላጠፈ መንገድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆናቹ ዜጎች እንኳን ደስ ያላችሁ። በሃገር ውስጥ የስራ ስምሪት ደግሞ በቅርብ ግዜ በሞባይል አፕሊኬሽን የታገዘ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የስራ አዋጪነት ኢንተርፕራይዝ ማደራጀትን የሚደግፍ፣ ከሰው ንክኪ ነጻ በሆነ መልኩ የስልጠና እና ሌሎች ልዩ ልዩ ድጋፎችን መስጠት የሚያስችል የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓቱ አካል የሆነ ስርዓት ለምቶ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል። ይሄንን መረጃ አውቃችሁ በየ አከባቢው እየተከፈቱ ባሉ የአሻራ መስጫ ማዕከላት ቀርባቹ መረጃዎቻቹን በመሙላትና አሻራ በመስጠት የስርዓቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። የምዝገባ ሂደቱን ለማየት: https://youtube.com/@BequELMIS?si=vxFnJR9VdCCdbQwR ለመመዝገብ: https://lmis.gov.et
en_USEN
Scroll to Top