Mols.gov.et

ፕሮጀክቱ ብቁ እና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን ለሥራ ገበያው ለማቅረብ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

November 6, 2025
ፕሮጀክቱ ብቁ እና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን ለሥራ ገበያው ለማቅረብ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው ትምህርትና ስልጠና ለሥራ ሥምሪት ፕሮጀከት (EASE Project) የአፈጻጸም ግምገማ እና ስልጠና መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በመድረኩ ፕሮጀክቱ ከሚተገበርባቸው የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተውጣጡ አስተባባሪዎች እና የሥራ ቦታ ደህንነት ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ሐፍቶም ገ/እግዚያብሔር(ረ/ፕሮፌሰር)፣ ፕሮጀክቱ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በሥራ ገበያው ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆኑ ሰልጣኞች እንዲያፈሩ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ በቀጣይ ፕሮጀክቱ የሥራ ጥራት ላይ እንደሚያተኩር የተጠቆመ ሲሆን አዳዲስ የሚጀመሩ እና የሚሻሻሉ ፕሮግራሞች ላይ ውጤታማ አፈጻጸም እንዲመዘገብ የጋራ አረዳድ ለመፍጠር መድረኩ መዘጋጀቱ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ወደ ሥራ ሥምሪቱ የሚገቡ ሰልጣኞች የሥራ ቦታ ደህንነት የሚያረጋግጥ ሥራ በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝም አስተባባሪው ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በአለም ባንክ የፋይናንስ ድጋፍ እና በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስፈጻሚነት ሚኒስቴር መ/ቤቱን ጨምሮ በ24 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
en_USEN
Scroll to Top