Mols.gov.et

ጠንካራ የሙያ ብቃት ምዘና ሥርዓት፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ፤ ጠንካራ ሀገር!

June 8, 2026
ጠንካራ የሙያ ብቃት ምዘና ሥርዓት፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ፤ ጠንካራ ሀገር! የክህሎት ልማት ዘርፋችን ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን የማፍራት ሀገራዊ ተልዕኮውን በስኬት እንዲወጣ የሙያ ብቃት ምዘና ሚና የማይተካ ድርሻ አለው፡፡ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓታችን ተራ የፈተና ሂደት አይደለም፡፡ ይልቁንም ክፍተትን ለይቶ መሙላት እንዲቻልና የዜጎችን ክህሎት ወደ ላቀ ምርታማነት፣ ምርታማነትን ደግሞ ወደ ሀገራዊ እድገት የሚቀይር የሰው ሀብት ልማታችን ዋነኛ የጥራት ማረጋገጫ መሣሪያ ነው! ይህንን ሀገራዊ ሥርዓት ይበልጥ ዘመናዊ፣ ተደራሽ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ከኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ጋር ሙሉ በሙሉ የማስተሳሰር እና የዲጂታላይዝ የማድረግ ሥራ ተጠናቋል። በዚህም፦ ⚡ የምዘናና የብቃት ማረጋገጫ ሂደቱ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ምቹ እንዲሆን እና 🛡️ በዘርፉ ይስተዋሉ የነበሩ የአሠራር ክፍተቶችን እና ብልሹ አሠራሮችን ከመሠረቱ የሚቀይር ግልጽ ሥርዓት ለመፍጠር ያስችላል። ይህንን ሁሉን አቀፍና ደረጃውን የጠበቀ ሥርዓት በመላው ሀገሪቱ ለማስፈን አስቻይና ሰፊ መዋቅር በየደረጃው አለ። በእስካሁኑ ሂደትም፦ 🏢 14 የክልልና ከተማ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘና ኤጀንሲዎች/ባለሥልጣናት፣ 🎯 1,843 የምዘና ማዕከላት በመላው ሀገሪቱ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። እነዚህ 14 የክልልና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮቻችን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል፣ ወደ ዓለም አቀፉ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት (Quality Management System – ISO) እንዲገቡ የማድረግ ሰፊ ሥራም እየተከናወነ ይገኛል። በዚህ ቀጣይነት ባለው ጥረት እስካሁን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችንን እና ተጠሪ ተቋሞቻችንን ጨምሮ በዘርፋችን የዓለም አቀፉን የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት እውቅና ያገኙ ተቋማት ቁጥር ከ20 በላይ ደርሷል።
en_USEN
Scroll to Top