Mols.gov.et

“የጥናትና ምርምር ሥራዎች ፋይዳ የሚኖራቸው ወደ ተግባር መሸጋገር ሲችሉ ነው፡፡”

July 12, 2024
“የጥናትና ምርምር ሥራዎች ፋይዳ የሚኖራቸው ወደ ተግባር መሸጋገር ሲችሉ ነው፡፡” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩና በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲቲዩት የተጠኑ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የሚኒስቴሩ ካውንስል አባላት እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡ በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለፁት፤ የተጠኑ ጥኖቶች እቅዶቻችን ላይ እሴት መጨመር በሚያስችል መልኩ መተግበር አለባቸው። ጥናቶች ፋይዳ የሚኖራቸው ወደ ተግባር መሸጋገር ሲችሉ ነው ብለዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) በበኩላቸው ጥናቶቹ እንደ ሀገር እጅግ ወሳኝ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ጠቅሰው ወደ ተግባር መሸጋገር እንዲችሉ ወደ ስርዓት ትምህርት እየቀየሩ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የጥናትና ምርም ስራዎቹ በሦስት ርዕሰ ጉዳዮች (Technology Mapping on Prioritized Government Development Sectors, Study on TV related Indigenous Knowledge and Skills in Ethiopia and Implementation of Zoning and Differentiation Initiatives: Brief Assessment) ያተኮሩ ናቸው፡፡
en_USEN
Scroll to Top