Mols.gov.et

የጋራ ትብብሩ ፓን አፍሪካኒዝምን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው፡፡

July 27, 2024
የጋራ ትብብሩ ፓን አፍሪካኒዝምን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ልዩ አማካሪ ትራወሬ አኖውሳ የተመራ የልዑካን ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ በክህሎት ልማት፣ ኢንተር ፕሪነርሺፕ እና መሰል ዘርፎች ላይ ልምድ ለመለዋወጥና በትብብር ለመስራት ባለመው ውይይት ቡርኪና ፋሶ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት ለመስራት እንደምትፈልግ አማካሪው ጠቁመዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያ በሚሰጠው የሀገራችን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ቀጠናውን በልማት ሊያስተሳስሩ በሚያስችሉ ጉዳዮች በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳንና ለሱማሊያ በሰጠቸው የትምህርትና ስልጠና ዕድል ከ250 በላይ ሰልጣኞች በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ይገኛል ብለዋል፡፡ በኢፌዴሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ስር በሚገኘውና ዓለም አቀፍ እውቅና ባገኘው የቴክኖሎጂ ፋብሪኬሽንና የብየዳ ልህቀት ማዕከል ውስጥ የትምህርት ዕድሉ ተጠቃሚዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን እየወሰዱ እንደሚገኝ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ከቡርኪና ፋሶ ጋር መሰል ትብብር እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡ ይህም በጋራ አብሮ ከመልማት ባሻገር ፓን አፍሪካኒዝምን ይበልጥ የሚያጠናክር እንደሆነም ክብርት ሚኒስትር አመላክተዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top