Mols.gov.et

የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል እና ሠላማዊ ኢንዱስትሪ የመፍጠር ሥራዎች የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ ተገለፀ

July 20, 2024
የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል እና ሠላማዊ ኢንዱስትሪ የመፍጠር ሥራዎች የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ ተገለፀ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር የሚመክርበት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም የትምህርትና ስልጠና እና የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፖሊሲዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ የበለፀገ ማህበረሰብ እና ሀገር ለመገንባት የትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡ ከዚህ አንፃር ከስልጠና በላይ በሚል የክህሎት ልማት ዘርፉ አዲስ እሳቤ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ዜጎችን ክህሎት ከማስታጠቅ አልፈው የትምህርትና ሥልጠና ጥራቱን በሚያረጋግጥ መልኩ የተለያዩ ሥራዎችን እንዲሰሩ፤ ተኪ ምርቶችን እንዲያመርቱና ህብረተሰቡንም ተጠቃሚ እንዲያደርጉ እየተሰራ ያለው ሥራ እጅጉን የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡ በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉም ሚኒስቴሩ ሥራ ዕድል በመፍጠር ብቻ ሳይሆን ስነ-ምህዳሩንም ምቹ ከማድረግ እንዲሁም በሠላማዊ ኢንዱስትሪ ከመፍጠር አኳ እጅግ ወሳኝ የሚባሉ ውጤቶችን እያመጣ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፤ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት ዓመታት በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል እና ሰላዊ ኢንዱስትሪ ለመፍጠር በትኩረት ሲሰራ የቆየ ሲሆን በዚህም ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል፡፡ የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል እና ሠላማዊ ኢንዱስትሪ የመፍጠር ሥራዎች የሁሉንም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር የተከበረው የምክርቤት አባላት ይህንን ከግምት በማሰገባት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያድጉ ጠይቀዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top