Mols.gov.et

የኢፌዴሪ ተክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የአይሶ 9001፡2015

August 6, 2024
የኢፌዴሪ ተክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የአይሶ 9001፡2015 የጥራት ሥራ አመራር ሰርተፍኬት ባለቤት ሆነ፡፡ የጥራት ሥራ አመራር ሰርተፍኬቱ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ እንየው ለኢፌዴሪ ተክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) አስረክበዋል፡፡ በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ኢኒስቲትዩት በአይሶ 9001፡2015 የጥራት ሥራ አመራር የተቀመጡ መስፈርቶች አሟልቶ የሰርተፍኬት ባለቤት በመሆኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በተቋሙ ጥራት ቀጣይነት ባለው መልኩ ባህል እንዲሆን መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ ሚኒስቴሩ በየደረጃው የሚገኙ ተቋማትና ባለሙያዎች ጥራት ባህላቸውን ያደረጉ፣ ራሳቸውን ያዘመኑና ከወቅቱ ጋር የሚራመዱ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ሰርተፍኬት ባለቤት መሆን የተቋማቱ እና ከተቋመቱ የሚወጡ ባለሙያዎች በየትኛውም አለም ተቀባይነት እንዲኖራቸው እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡ የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) በበኩላቸው ተቋሙ የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ሰርተፍኬት ባለቤት መሆኑ የአሰራር ወጥነት እንዲኖር፣ የሰራተኛ ብቃት ለማሳደግ፣ ምርታማነትን ለመጨመር እና የኢንስቲትዩቱን ግብ ለማሳካት ያለው ፋይዳ የጎላ ገልጸው ለስኬቱ አስተዋጽዎ የነበራቸው አካላትን አመስግነዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top