Mols.gov.et

የኢንተርፕረነርሺፕ ስነምህዳር ለመገንባት ትልቅ ልብ እና ደፋር አመራር የስፈልጋል ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

November 18, 2025
የኢንተርፕረነርሺፕ ስነምህዳር ለመገንባት ትልቅ ልብ እና ደፋር አመራር የስፈልጋል ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዓለም አቀፍ ኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት በኢትዮጵያ ይፋዊ የመክፍቻ ስነ-ስርዓት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ አለም አቀፍ ተሳታፊ እንግዶች እና የዘርፉ ተዋንያን በተገኙበት ተከፍቷል፡፡ መርሃ ግብሩን በይፋ የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ መንግስት በኢትዮጵያ የኢንተርፕረነርሺፕ ስነ-ምህዳር እንዲሰፋ ካለው ከፍተኛ ቁርጠኝነት በመነሳት ዘርፉን የሚመራ ተቋም ከማቋቋም ጀምሮ አዳዲስ አሰራሮችን እየተገበረ ይገኛል ብለዋል፡፡ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) ጀምሮ ለዘርፉ እድገት በተሰጠ ቆራጥ አመራር ኢትዮጵያ በአለም መድረክ በዘርፉ ባስመዘገበችው ውጤት ስሟ ከፊት እንዲነሳ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ ኢንተርፕረነርሺፕ ለግሉ ዘርፍ የተተወ ከነበረበት ወደ መንግስት ተቋማት በማምጣት፤ ኢንተርፕረነር የሆኑና ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ የጀመሩ ተቋማት መታየት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡ የኢንተርፕረነርሺፕ ስነምህዳር ለመገንባት ትልቅ ልብ እና ደፋር አመራር የስፈልጋል ያሉት ክብርት ሚኒስትር የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩትም በዚህ ቅኝት ስለተመራ በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ በርካታ በአይቻልም አስተሳብ የታሰሩ አዕምሮዎች ነጻ እንዲወጡ በር ከፍቷል ብለዋል፡፡ የኢንተርፕረነርሺፕ ስነምህዳር ለመገንባት ሁሉም ባለድርሻ አካላት እጅ ለእጅ ተያይዘን ከተጓዝን ኢትዮጵያን የኢንተርፕረነሮች መፍለቂያ እናደርጋታለንም ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top