Mols.gov.et

የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር…

August 3, 2024
” #ክሂሎት ” ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ፣ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ በነበሩበት ወቅት “ክሂሎት” በሚል ርዕስ መፅሀፍ ማሳተማቸው ይታወቃል። ይህንኑ መፅሀፋቸውን ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ በመተርጎም በድጋሜ አሳትመዋል:: ይህንን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዕትም ሚንስትር መስሪያ ቤቱ በክህሎት ልማት ዘርፉ በማጣቀሻነት እንዲያገለግል ለሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አስረክበዋል። ክብርት ሚኒስትር መፅሀፉን በተረከቡበት ወቅት እንደገለፁት፣ ክህሎት ከፍላጎትና ምኞት ወደ ስኬት የመሻገሪያ ድልድይ ነው:: የብዙዎችን ምኞት እና ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት በክህሎት ልማቱ ዘርፍ መሰል የማጣቀሻ መጽሀፍት ከፍተኛ ሚና ያላቸው ቢሆንም በሀገራችን ምሁራን የተዘጋጁ ማግኘት ቀላል አይደለም። ፀሀፊው ዘርፉን የመሩና እንደ ሀገር በመስኩ ያሉ ዕድሎችንና ተግዳሮቶችን በአግባቡ የለዩ እንዲሁም በመስኩ ያካበቱትን ሰፊ ልምድ ያካፈሉበት እንደመሆኑ ለዘርፉ ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል። ባላቸው የተጣበበ ጊዜ ይንን መጽሐፍ በማዘጋጀት ለንባብ በማብቃታቸው ያላቸውን አድናቆት የገለፁት ክብርት ሚኒስትር መጽሐፉን ለዘርፉ በማበርከታቸው ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል።
en_USEN
Scroll to Top