Mols.gov.et

የአፍሪካ ልማት ባንክ ልዑካን ቡድን ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡

January 17, 2025
በአፍሪካ ልማት ባንክ የግሉ ዘርፍ፣ መሠረተ ልማትና ኢንዱስትሪያላይዜሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር ሰለሞን ኩይኖር ከተመራው የአፍሪካ ልማት ባንክ ልዑካን ቡድን ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡ በውይይቱ በግብርናው ዘርፍ የሚሰሩ ኢንተርፕራይዞችን በማጠናከር ለዜጎች ሰፊና ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር በኢትዮጵያና በአፍሪካ የልማት ፈንድ መካከል በተፈረመው ስምምነት መሰረት የተከናወኑ ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ መመልከታቸውንና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችንም ማስቀመጣቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል፡፡ በአፍሪካ ልማት ባንክ የግሉ ዘርፍ፣ መሠረተ ልማትና ኢንዱስትሪያላይዜሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር ሰለሞን ኩይኖር እና የልዑካን ቡድን አባላት ለስምምነቱ ተግባራዊነት እያደረጉ ላለው ጠንካራ ድጋፍና ክትትልም አመስግነዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top