Mols.gov.et

የሥራ ምህዳሩን ለማስፋት፣ ሁሉን አቀፍ ጥረት !

July 18, 2024
የሥራ ምህዳሩን ለማስፋት፣ ሁሉን አቀፍ ጥረት ! የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩ ምቹ ምህዳር መፍጠር የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም ሥራዎች መካከል ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበትና የሚሸጡበት ሉሲ የተሰኘ የዲጂታል ሥርዓት በዋናነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ይህ ስርዓት በውስጥ አቅም በልጽጎ ወደ ሥራ የገባው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ውስጥ ከሚካተቱ 22 በላይ አገልግሎት መካከል አንዱ ሲሆን ለኢንተርፕራይዞች ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለውና የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ነው፡፡ ስርዓቱ በበዓላት ኤግዚቢሽንና ባዛሮች እንዲሁም የሰንበት ገበያዎች ተወስኖ የነበረውን የኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎት የማስተዋወቅ ሥራን የሚያሳድግ እና ኢንተርፕራይዞቹ ወቅቱን የዋጁ የገበያ አማራጮች እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው፡፡ ከዲጂታል መሰረተ ልማቱ ጎን ለጎን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአይነቱ ልዩ የጥራት ሰርተፊኬት ያወጡና ከመላ ሀገሪቱ የተመረጡ ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ የሚሸጡበት እና የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት የኢንተርፕራይዞች ህንፃ (Emporium) በመዲናችን አዲስ አበባ እያስገነባ ይገኛል፡፡ ይህ ስፍራ በከተማው አንዱ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆንም ታስቦ የሚገነባ ነው፡፡ ግንባታው አሁን የደረሰበትን ደረጃ ክብርት ሚኒስትር ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሚኒስትር ዴኤታዎችና ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የጎበኘ ሲሆን ግንባታው በተያዘለት እቅድ በጥራት እንዲጠናቅ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
en_USEN
Scroll to Top