Mols.gov.et

የሥራ ማዕከላት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል የሚሳለጥባቸው ወሳኝ …

April 22, 2026
የሥራ ማዕከላት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል የሚሳለጥባቸው ወሳኝ ድልድዮች ናቸው፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፤ ከአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ጆዜፍ ሲኬላ እና የስዊድን የፍልሰት ሚኒስትር ጆሃን ፎርሴል የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ወረዳ 12 ቦሌ ቡልቡላ የሥራ ማዕከል ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የሰው ኃይሏን ወደ ውጤታማ ሀብት ለመቀየርና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የቴክኒክና ሙያ ተቋማትንን እንደ ግብርና፣ ማዕድንና ኢንዱስትሪ ካሉ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር አስተሳስራ እየተገበረች ትገኛለች፡፡ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ መሠረት፣ በ2018 በጀት ዓመት (2025/26) ብቻ 5.6 ሚሊዮን አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ሰለሞን፤ የሥራ ማዕከላት ደግሞ ይህንን ግብ ለማሳካት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል የሚሳለጥባቸው ወሳኝ ድልድዮች ናቸው ብለዋል። የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት በኢትዮጵያና በአውሮፓ ሕብረት መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ጠቁመው ለዚህም የሰለጠነ የሰው ኃይልን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ከአለም የሥራ ድርጅት (ILO) እና ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑ ጨምረው ገልጸዋል። በጉብኝቱ ላይ የአውሮፓ ሕብረትና የስዊድን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮች እንዲሁም የILO እና IOM መሪዎች የተገኙ ሲሆን፤ የልዑካን ቡድኑ በሥራ ማዕከሉ ያለውን አገልግሎትና የዲጂታል አሠራር ተመልክቷል።
en_USEN
Scroll to Top