Mols.gov.et

የሥራ ማዕከላትን ተደራሽነትን ለማሳደግና ለማጠናከር …

December 18, 2025
የሥራ ማዕከላትን ተደራሽነትን ለማሳደግና ለማጠናከር ቢሮው በትኩረት እየሰራ እንደሆነ አስተዋቀ የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ማዕከላትን ተደራሽነትን ለማሳደግና ለማጠናከር በትኩረት እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ የቢሮ ምክትል ኃላፊና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለዉ ከበደ እንደገለፁት፤ የሥራ ማዕከላት የሥራ ፈላጊ ዜጎች የሚመዘገቡባቸው፣ ኢንተርፕራይዞች የሚፈልቁባቸውና አስፈላጊውን መንግስታዊ ድጋፍ የሚያገኙባቸው ሥፍራዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ቢሮው ለሥራው ልዩ ትኩረት በመስጠት በሁሉም አካባቢ ተደራሽ እንዲሆኑ እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡ በእስካሁኑ ሂደት ህብረተሰቡን በማስተባበር 86 የሚሆኑ አዳዲስ የሥራ ማዕከላት እየተገነቡ እንደሚገኙ ጠቁመው በቅርቡ ተጠናቀው ለሥራ ክፍት እንደሚሆኑም አስረድተዋል፡፡ ተደራሽነቱን ከማስፋት ባሻገር የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ ማዕከላቱን በቴክኖሎጂና በመሰረተ ልማት የማሟላትና በብቁ የሰው ሃይል እንዲደራጁ የማድረግ ሥራም እየተሰራ መሆኑን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሥራ ዕድል የተቀመጡ ግቦቹን ለማሳካት ለማሳካት ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል ሥራ ፈላጊዎችን የመመዝገብ፣ የማደራጀትና መንግስታዊ ድጋፎችን የማመቻቸት ተግባራትን የሚያከናውኑ የሥራ ማዕከላትን ማጠናከር በዋነኛነት ይጠቀሳል፡፡ በዚሁ መሰረት ማዕከላቱ ለሥራ ፈላጊ ዜጎች ፈጣን፣ ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ማዕከላቱን ሪፎርም የማድረግ ሥራ በክልሎች በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡
en_USEN
Scroll to Top