Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተግባራዊነትን …

April 15, 2024
የመስክ ምልከታው በዘርፉ በአፈፃፀም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታትና ምርጥ አሰራሮችን ለይቶ ማስፋት በሚያስችል መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቆመ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተግባራዊነትን ለመከታተልና ለመደገፍ በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራ የልዑካን ቡድን በክልሎችና በከተማ አስተዳድሮች የመስክ ምልከታ እያደረገ ነው፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የመስክ ምልከታውን ሂደት ሥራው ከሚመሩ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ገምግመዋል። በበይነ መረብ በተደረገው በዚህ መድረክ የመስክ ምልከታው በታቀደው ዕቅድ መሰረት እየተከናወነ ነው። ከክልል ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የመስክ ምልከታ የአንድ ማዕከላትና ማሰልጠኛ ተቋማት ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አስፈፃሚ አካላት ጋር ውጤታማ ምልከታ እየተደረገ ነው። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የመስክ ምልከታው በዘርፉ በአፈፃፀም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታትና ምርጥ አሰራሮችን ለይቶ ማስፋት በሚያስችል መልኩ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በሂደቱም የታዩ ክፍተቶችን መሙላት የሚያስችል ልዩ ዕቅድ ተዘጋጅቶ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
Scroll to Top

The Ministry of Labor & Skills