Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የበጀት ዓመቱን የአምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እና የሪፎርም ሥራዎች

December 20, 2024
መድረኩ በበጀት ዓመቱ ያስቀመጥናቸውን ግቦች ያሉበትን ደረጃ በመፈተሸ አፈፃፀማችንን ለማላቅ ትልቅ ዕድል የሚሰጠን ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የበጀት ዓመቱን የአምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እና የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም ላይ ያዘጋጀውን የውይይት መድረክ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለፁት መድረኩ በበጀት ዓመቱ ያስቀመጥናቸውን ግቦች ያሉበትን ደረጃ በመፈተሸ አፈፃፀማችንን ለማላቅ ትልቅ ዕድል የሚሰጠን ነው፡፡ የድጋፍና ክትትል ቡድን እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ወርዶ ስራዎችን እንደተመለከተ ገልጸው በዚህም ከሀገራዊ ሪፎርም ጋር በተጣጣመ መልኩ ሚኒስቴሩ ያወረዳቸው የሪፎርም ሥራዎች ፍሬ ማፍራት መጀመራቸውን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል፡፡ በድጋፍና ክትትል ቡድኑ እና በዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ከቦታ ቦታ የአፈጻጸም ልዩነት መኖሩን በግልጽ መታየቱን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በቀጣይ እነዚህን ተቋማት ወደ ተቀራረበ አፈጻጸም ለማምጣት በትኩረት እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከክህሎት ልማት፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ከአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት፣ ከተቋም ግንባታ፣ ከሙያ ብቃት ምዘና አኳያ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና የሱፐርቪዥን ሪፓርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው፡፡ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው በዚህ መድረክ ከውይይቱ ባሻገር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አካል የሆኑና የማበልፀግ ሥራቸው የተጠናቀቁ የዲጂታል ስርዓቶች ይፋ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
en_USEN
Scroll to Top