Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲያከናውናቸው የነበሩ የክረምት የበጎ ፈቃድ …

August 12, 2024
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲያከናውናቸው የነበሩ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የልማት ስራዎች በማጠናቀቅ አስረከበ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ልማት ሥራዎች ሲያከናውናቸው የነበሩ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ እና ማስፋፍያ ሥራ እንዲሁም የመኖሪያ ቤት ግንባታ ስራ በማጠናቀቅ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በተገኙበት በዛሬ ዕለት ርክክብ ተደርጓል። በርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ እንደገለጹት፤ በፌዴራል ደረጃ አሁን የተጀመረው የመተጋገዝ ባህል ተጠናክክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን ገልጸው ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል። ከለውጡ በኋላ በክልሉ በርካታ ውጤታማ የልማት ስራዎች መከናቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ድጋፋም የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን የሚያጠናክር ነው ብለዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራው የትምህርት ቤት ማስፋፊያ እና የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ በማከናወን ርክክብ መደረጉን ገልጸው ድጋፋ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በተጨማሪም ሁለት ሺህ ለሚሆኑ ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንም ገልጸዋል። የተደረገው ድጋፍም የርስበርስ የመተሳሰብና የመደጋገፍ ባህላችን የሚያጎለብት ከመሆኑ ባሻገር በተለይ የተገነቡት ቤቶች በአነስተኛ ዋጋ በአዲስ ቴክኖሎጂ የተሰሩ በመሆኑ ለቴክኖሎጂ ሽግግር ያለው አስተዋጽዎ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። ቴክኖሎጂው ቤት በአነስተኛ ወጪ እና ባጠረ ጊዜ ማጠናቀቅ የሚያስችል በመሆኑ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ያስችላል ብለዋል። በአሁን ወቅት በክልሉ በዚህ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሰልጥነው የተደራጁ አራት ኢንተርኘራይዞች እንቅስቃሴ መጀመራቸውንም ጠቁመዋል።
en_USEN
Scroll to Top