Mols.gov.et

ኮሌጁ ለአካባቢው አርሶ አደሮች እና ለተደራጁ ወጣቶች ..

July 13, 2024
ኮሌጁ ለአካባቢው አርሶ አደሮች እና ለተደራጁ ወጣቶች የተሻሻሉ የእንስሳትና የዕጸዋት ዝርያዎችን እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ የአላጌ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ኮሌጅ የተሻሻሉ የእንስሳትና የዕጸዋት ዝርያዎችን ለአርሶ አደሮች እና ለተደራጁ ወጣቶች መሰጠቱን አስታወቀ፤ በአላጌ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንተርፕራይዝ ምክትል ዲን የሆኑት ትምህርቱ ሳህሉ (ዶ/ር) እንደገለጹ፤ በትምህርት ማሰልጠኛ ኮሌጁ ውስጥ ከማሰልጠን በተጨማሪ የተለያዩ የምርምርና ጥናቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡ በጥናትና ምርምር ማዕከላቱ የአየር ንብረትን መቋቋም የሚችሉ የአትክልትና የፍራፍሬዎች ችግኞችን የማፍላት ሥራ ተሰርቷል፡፡ 150 ለሚደርስ አርሶ አደሮች ተገቢ የሆነ ሥልጠና እንዲያገኙ በማድረግም የተሻሻሉ የኮርማ፣ የፍየልና የጊደር ዝርያዎችን እንዲሁም ዘመናዊ የንብ ቀፎዎችን እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ከ3 ቀበሌ ለተውጣጡ 30 ወጣቶች የኦርጋኒክ ኮምፖስት ማዳበሪያ አዘገጃጀት ሥልጠና መስጠቱንም ነው የኮሌጁ ም/ል ዲን ያመላከቱት፡ በዚህ ዓመት በ6 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት እና በ3 የወረዳ ከተሞች አስከ ሰባት መቶ አምሳ ሽህ የሚደርሱ የተለያየ ዝርያ ያላቸው የሙዝ፣ የቡና፣ የፓፓያ፣ የሞሪንጋ እና ሌሎች ሀገር በቀል የዛፍ ችግኞችን በማዘጋጀት ወደ ህብረተሰበቡ ለማድረስ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡ ዶክተር ትምህርቱ አክለውም የኮሌጁንና የአካባቢውን ማህበረሰብ በጋራ የሚያስተባብር ልዩ ኮሚቴ መቋቋሙን ጠቁመው ሃምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም የኮሌጁንና የአካባቢውን ማበረሰብ የሚያሳትፍ የችግኝ ተካላ ፕሮግራም ይካሄዳል ብለዋል ፡፡
en_USEN
Scroll to Top