Mols.gov.et

“ከፈጠራ ሐሳብ ወደ ተጨባጭ ተግባር’’

March 26, 2026
“ከፈጠራ ሐሳብ ወደ ተጨባጭ ተግባር’’ የክህሎት ባንክ የሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን ችግር ፈቺ ተግባር በማሸጋገር ረገድ ከፍተኛ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለፀ፡፡ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም በሆነው በኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ስር የሚገኘው “የክህሎት ባንክ” (Skill Bank)፣ የፈጠራ ስራዎችን በማልማትና ወደ ንግድ ማዕቀፍ (Commercialization) በማሸጋገር ረገድ ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበ ይገኛል፡፡ ማዕከሉ በተለይ በክረምት መርሃ-ግብር እና በ“ስኪል ኢትዮጵያ ስታርታፕ” ፕሮግራም የለሙ ቴክኖሎጂዎችን ለገበያ በማቅረብ ለሀገራዊ ምርታማነት የላቀ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ነው፡፡ የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፀዳለ ተክሉ እንደገለጹት፤ ስኪል ባንክ ከመረጃ ቋትነት ባለፈ አዳዲስ የፈጠራ ሐሳቦች ተቀርጸው ወደ ተግባር የሚቀየሩበት ህያው የፈጠራ መድረክ (Innovation Hub) ነው ። እስካሁንም ከ600 በላይ ወጣቶችን በማሳተፍ ከ160 በላይ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲፈጠሩ ያደረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በርካታ ተኪ ቴክኖሎጂዎች ወደ ተጠቃሚው ማህበረሰብ እየደረሱ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ወይዘሮ ፀዳለ ገለጻ፣ በማዕከሉ ከለሙና ወደ ንግድ ከተሸጋገሩ ስኬታማ ቴክኖሎጂዎች መካከል በኢንተርኔት የታገዘ ስማርት መስኖ (IoT Smart Irrigation) በአፋርና ሶማሌ ክልሎች በንግድ ደረጃ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን፣ አፈር አልባ የሆነው የ”ሃይድሮፖኒክ” የእንስሳት መኖ ማምረቻ ቴክኖሎጂም ከኢንተርፕራይዞች ጋር በተፈጠረ ትስስር ምርቱን በስፋት እያቀረበ ይገኛል።
en_USEN
Scroll to Top