Mols.gov.et

ኢፍጣር፤ የአብሮነት መገለጫ!

March 17, 2026
ኢፍጣር፤ የአብሮነት መገለጫ! የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው የጋራ የኢፍጣር መርሃ ግብር በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቅጽርግቢ ተካሄዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጨምሮ የባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ይህ የኢፍጣር መርሃ ግብር በረመዳን ወር የሚታዩትን የመረዳዳት፣ የመተሳሰብ እና የመካፈል ታላላቅ መንፈሳዊ እሴቶች መሠረት ያደረገ ነው። መሰል መርሃ ግብሮች በተቋሙ አመራርናሠራተኞች መካከል ያለውን አብሮነት በማጠናከር በመካከላቸው ያለውን ቤተሰባዊ ቅርርብን በማላቅ ለተቋማዊ ስኬትና ለሥራ ተነሳሽነት መሠረት የሚጥሉ ናቸው፡፡
en_USEN
Scroll to Top