ኢንስቲትዩቱ ያቋቋመውን የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ሥራ አስጀመረ
የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ያቋቋመውን የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ሥራ አስጀምሯል፡፡
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድርን ጨምሮ የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡
ዶ/ር ብሩክ ከድር ባስተላለፉት መልዕክት የቴክኒክና ሚያ ሥርዓቱን አካታች ማድረግ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ባሻገር በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ልማት ውስጥ ሁሉም ዜጎች ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ሥራ ያስጀመርነው ይህ ማዕከል ኢንስቲትዩቱ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሥልጠና ማዕከል ለመሆን ያለው ቁርጠኝነት ማሳያ እንደሆነም ገልፀዋል።
በኢንስቲትዩቱ ውስጥ አካል ጉዳተኝነት ከውጤታማነት ያላገዳቸው አሠልጣኞች፣ ተመራማሪዎች እና ቴክኖሎጂስቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡
በትምህርትና ሥልጠናው መስክ ማዕከሉ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ ከሌሎች ልምድና ተሞክሮዎችን የሚቀስሙበት ቦታም እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተመላክቷል፡፡