Mols.gov.et

ኢንስቲትዩቱ የዓለም አቀፍ ብየዳ የአሰልጣኞች ስልጠናን መስጠት ጀመረ

October 8, 2024
ኢንስቲትዩቱ የዓለም አቀፍ ብየዳ የአሰልጣኞች ስልጠናን መስጠት ጀመረ የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ማምረትና የብየዳ ልህቀት ማዕከል የዓለም አቀፍ ብየዳ የአሰልጣኞች ስልጠናን ዛሬ አስጀምሯል። በስልጠናው ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ 120 የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች እንደሚሳተፉ የማዕከሉ ሀላፊ ሰላሙ ይስሀቅ (ዶ/ር) ገልፀዋል። በሦስት ዙሮች በሚሰጠው በዚህ ስልጠና የተግባርና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና እንደሚሰጥ ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል። የብየዳ ልህቀት ማዕከል በኢትዮጵያና በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ተቋም ነው።
en_USEN
Scroll to Top