Mols.gov.et

ኢትዮጵያ በጄኔቫ እየተካሄደ ባለው 112ኛው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፈች ነው።

June 6, 2024
ኢትዮጵያ በጄኔቫ እየተካሄደ ባለው 112ኛው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፈች ነው። በጄኔቫ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ ባለው 112ኛው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ኮንፈረንስ ላይ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ በክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የሚመራ የልዑካን ቡድን በመሳተፍ ላይ ይገኛል። ሚኒስትር ዴኤታው በምልአተ ጉባኤው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ማህበራዊ ፍትህን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት እንዲሁም በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተከናወኑ ሌሎች ተያያዥ የሪፎርም ሥራዎችን አንስተዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ተግባራዊ በማድረግ ላይ የምትገኘው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እና ከዘላቂ ልማት ግቦች ጋር የሚጣጣም መሆኑን ጠቁመው አበረታች ውጤት እየተገኘ እንደሆነም አንስተዋል፡፡ በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት ላይ ትልቅ ፋይዳ ያለውን የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓትን ጨምሮ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና የኢንዱስትሪ ሰላምን በማረጋገጥ ምርታማነትን ለማሻሻል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በመድረኩ ላይ ጠቁመዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top