አገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራት ጥናት ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ
በትምህርትና ስልጠና ፓሊሲ እና በዘርፉ ስትራቴጂዎቻችን እንደተመላከተው፣ የተለያዩ የጥናት ሰነዶችም ላይ እንደሚጠቀሰው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ሊለወጥ ከሚገባቸው ጉዳዮች መካከል የጥራት ጉዳይ ዋነኛው ነው።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር የጥራት ጉዳይ እንዲሳካ በመጀመሪያ ችግሮችን መለየትና ማሳኪያ መንገዶችን ማጥናት ይገባል ብለዋል።
የጥናት ቡድኑን ስምሪት የሠጡት ዋና ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ ባሳለፍነው ዓመት የስልጠና ጥራትን የተመለከተ የውስጥ ጥናት ማድረጉን በዚህም በርካታ ግኝቶች መገኘታቸውን አስታውሰው ከዚህ ግብአት በመነሳት በአገርአቀፍ ደረጃ ያለውን ስልጠና ጥራት ማጥናት ማስፈለጉን ገልጸዋል።
ዓላማውም የቴክኒክና ሙያ የጥራት ጉዳይ ፈተናዎቹ ምንድን እንደሆኑ መለየት፤ የባለድርሻ አካላትን ሚና በተተነተነ ሁኔታ መለየት እንዲሁም ተቋማት በተናጠል ጥራትን ለማስጠበቅ እየሰሯቸው ያሉ ስራዎችን ለመለየት እንደሆነ ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም በዚህ ጥናት ሁሉም አካባቢዎች ሁሉም ባለድርሻዎች እንዲሳተፉ ይደረጋል ብለዋል።
በጥናት ቡድኑ ስምሪት ላይ የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሐብታሙ ሙሉጌታ ተገኝተዋል።