Mols.gov.et

አዳዲስ የትብብር መስክ የከፈተ…

May 22, 2025
አዳዲስ የትብብር መስክ የከፈተ… የ20ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች በዘርፋችን የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ አዳዲስ የትብብር መስክ ፈጥሯል:: በጉብኝቱ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሌበር ዘርፍ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የዓለም የሥራ ድርጅት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተካፍለዋል፡፡ በዚህም ለአፍሪካውያን የስልጠና እድል እየሰጠ በሚገኘው የኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የክህሎት ባንክን ተመልክተው ሥራውን አበረታተዋል፡፡ አድናቆትም ችረዋል፡፡ ዘመኑን በዋጁ የስልጠና ቁሳቁሶች የተደራጀውን የሮቦቲክስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የስልጠና ክፍሎችንም ተዘዋውረው ያዩ ሲሆን የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓትንም በዝርዝር ተመልክተዋል፡፡ በጋራ መሥራት የሚቻልበት አግባብ ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡ የአፍሪካን የተሟላ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እንደ “ክህሎት ኢትዮጵያ” ያሉ መርሃ ግብሮችና መሰል የልምድ ልውውጥ መድረኮች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በውይይታችን ወቅት በጉልህ ተነስቷል፡፡ መርሃ ግብሩን ላመቻቹ፣ ላስተባበሩና ለመሩ የውጭ ጉዳይ፣ የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤታችንና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ! የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
en_USEN
Scroll to Top