Mols.gov.et

ችግሮችን የሚፈቱ እና የዘርፉን ለውጥ የሚያፋጥኑ ጉዳዮች ላይ …

March 24, 2024
” ችግሮችን የሚፈቱ እና የዘርፉን ለውጥ የሚያፋጥኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እንሰራለን።” የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ቲንክታንክ (ሀሳብ አመንጪዎች)ቡድን አባላት ከመላው ዓለም በተሰባሰቡ ከፍተኛ ልምድና ዕውቀት ያለቸው ሰዎችን በማካተት የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ቲንክታንክ ቡድን በያዝነው ዓመት ታህሳስ ወር ላይ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወሳል። ቡድኑ ሲቀቋም በዘርፉ የፖሊሲ አተገባበር ሂደት ሀሳብ በመስጠት እና ልምዶችን በማካፈል እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ተሞክሮዎችን በማምጣት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ጥራት ለማስጠበቅ ከፍተኛ እገዛ እንዲያደርግ ታሳቢ በማድረግ ነው። በአገራችን በአይነቱ የመጀመሪ የሆነው ይህ የቴክኒክና ሙያ ቲንክታንክ ቡድን አባላት ሁለተኛ መደበኛ ውይይታቸውን ሰሞኑን አካሂደዋል፡፡ በቀጣይ ስድስት ወራት የሚሰራቸው ተግባራት ላይ ትኩረት ያደረገው ቡድኑ ችግሮችን የሚፈቱና የዘርፉን ለውጥ የሚያፋጥኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እንሠራለን ብለዋል::
Scroll to Top

The Ministry of Labor & Skills