በወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በማህበር ለተደራጁ
May 12, 2026
በወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በማህበር ለተደራጁ ለ90 ወጣቶች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የመሸጫና የመሥሪያ ቦታ ሼድ አስረክቧል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ጫላ ይህ ተራ ላሜራ ወይም የመሸጫና የመሥሪያ ቦታ ሳይሆን ትልቁ የቢዝነስ ማዕከል ይሆናል ብለዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ትልቁ ዕሳቤ የሰውን ህይወት መቀየርና ዜጋን ውጤታማ እንዲሆን ማድረግ ነው ብለዋል።
ሰው ምርታማነትና ፍሬያም እንዲሆን ማድረግ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ፋይዳ አለው ያሉት ኃላፊው፥ ስራን መፍጠር ምርታማነት ማሳደግ እንደሆነም ገልፀዋል።
የስራ ትንሽ የለውም ያሉት ኃላፊው፥ ወጣቶች ስራን ሳይንቁ መሰራትና መትጋት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ለወጣቱ ስራ ዕድልን ለመፍጠር የግሉ ሴክተርን ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት ኃላፊው፥ ስራ አጥነትን ለመቅረፍ እያንዱንዱ ሰው ምሳሌ የሚሆን ስራ በመሰራት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበትም አሳስበዋል።
ሥራ አጥነት ችግር ለመንግስት ብቻ ሸክም ሳይሆን ለሁሉም ነው ያሉት ኃላፊው፥ ወጣቶች ስራን እንዲፈጥሩ ማበረታታት ያስፈልጋል ብለዋል።
ወጣቶቹ በማደራጀት፣ በማሰልጠን እንዲሁም አስፈላጊውን ቁሳቁስ በማሟላት በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ርብርብ ያደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በየአካባቢው የሚገኙ ፀጋዎችና እምቅ አቅሞቻችን በመጠቀም ለወጣቱ የተለያዩ ስራ አማራጮችን ለመፍጠር ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበትም አሳስበዋል።
የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዘካሪያስ ጃታ የከተማው አስተዳደር ለወጣቱ ስራ ዕድል ለመፍጠር የ90 ቀናት ዕቅድ በማቀድ ስሰራ እንደቆየ አስታውሰዋል።
ወጣቶች በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍና የክህሎት ስራ ዕድል መፍጠሩን የገለጹት ከንቲባው፥ ይህ ለወጣቱ ተስፋ የሚጭር ነው ብለዋል።
በከተማው የሚገኙ ሌሎች ወጣቶች ተደራጅተው መንግስት ያመቻቸው የስራ ዕድል ተጠቅመው ለመሰራት ፍቃደኛ መሆናቸውንም ገልፀዋል።
በዘርፉ የተሰማሩ ወጣቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ይህ መነሻ ይሆናል ያሉት ከንቲባው፥ ሌሎች ትምህርት የሚሆን ስራዎች መሰራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ዘገባው የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው።



