Mols.gov.et

በኦሮሚያ ክልል ወጣቶችን በክህሎት በማብቃት ወደ ሥራ እንዲገቡ …

December 16, 2025
በኦሮሚያ ክልል ወጣቶችን በክህሎት በማብቃት ወደ ሥራ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ገለጸ ቢሮው የወጣቶችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የተግባርና የንድፈ ሀሳብ ስልጠናዎችን በቅንጅት እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል። “ዛሬን ለነገ” በሚል የብቃት ፕሮጀክት በአዳማ ከተማ የሥራ ላይ የተግባር ስልጠና የወሰዱ 1ሺህ 799 ወጣቶች ተመርቀዋል። የኦሮሚያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ እ/ር ኤባ ገርባ እንደገለፁት፤ ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በመቀናጀት ወጣቶችን በክህሎት ለማብቃት የአጫጭርና ረጃጅም ጊዜ ስልጠናዎች እንዲወስዱ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል። የሥራ ላይ ስልጠናው በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈና የወጣቶቹን የሥራ ተወዳዳሪነት ማሳደግ የሚያስችሉ መሆናቸውን አንስተዋል። በክልሉ የዚሁ ተግባር አካል የሆነው የወጣቶችን የሥራ ብቃት ማሳደግን ዓላማ ያደረገ “ዛሬን ለነገ” በሚል የብቃት ፕሮጀክት የሥራ ላይ ሙያዊ ስልጠና በአዳማ፤ በሻሸመኔ እና በጅማ መሰጠቱን ገልጸው፤ የዛሬው በአዳማ የተከናወነው ምረቃ የዚሁ ጥረት አካል ነው ብለዋል። የሥራ ላይ ስልጠናውን ከወሰዱ ወጣቶች መካከል 1,799 ውጤታማ በመሆናቸው በኢንዱስትሪዎች የመቀጠር ዕድል ማግኘታቸውንም ተናግረዋል። ዘገባው የኦሮሚያ ክልል፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ነው
en_USEN
Scroll to Top