Mols.gov.et

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ክቡር ቼን ሃይ ጋር በቅንጅት መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ወይይት ተካሄደ፡፡

September 28, 2024
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ክቡር ቼን ሃይ ጋር በቅንጅት መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ወይይት ተካሄደ፡፡ በውይይቱ ላይ የተገኙት ክብርት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት በቻይና እድገትና ልማት ውስጥ የቴክኒከና ሙያ ትልቅ አበርክቶ እንደነበረው እና ኢትዮጵያም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በያዘችው ጉዞ ዘርፉ የማይተካ ሚና እንዳለው ከግምት በማስገባት መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራው ያለውን ሥራ በዝርዝር ለአምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ቻይና ለኢትዮጵያ በዘርፉ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ክቡር አምባሳደሩ አረጋግጠውልኛል ብለዋል ፡፡ ከውይይቱ በኋላ በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በቻይና መንግስት ድጋፍ የተገነባውን የሉባን ወርክሾፕ የጎበኘን ሲሆን በቻይና መንግስት የትምህርት እድል ተሰጥቷቸው ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በበይነ መረብ አግኝተው ማናገራቸውንና ማበራታታቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ግንኙነት ከሁለቱ ሀገራት ባሻገር የቻይና አፍሪካን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድግ በመሆኑ በኢትዮጵያ የቻይና አምበሳደር ለክቡር ቼን ሃይ በትብብር አብሮ ለመስራት ላሳዩን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top