Mols.gov.et

በኢትዮጵያ የስታርትፕ ስነ-ምህዳርን ምቹ ለማድረግ …

July 24, 2024
በኢትዮጵያ የስታርትፕ ስነ-ምህዳርን ምቹ ለማድረግ እየተዘጋጀ ባለው የሕግ ማዕቀፍ ላይ ውይይት ተካሄደ እንደ ሀገር ፈጠራ በታከለበት አግባብ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ አንድን ችግር ለመፍታት የሚቋቋሙ ስታርታፖች የሚበረታቱበትና የሚደገፉበት የሕግ ማዕቀፍ አልነበረም፡፡ ይህን በመገንዘብ መንግስት ስታርት አፖችን በአግባቡ ማስተናገድ የሚያስችል ስነ-ምህዳር ለመገንባት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ(ዶ/ር) ከተመራ የልዑካን ቡድን ጋር ምህዳሩን ምቹ ለማድረግ እየተዘጋጀ ባለው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ የረቂቅ አዋጅ ዝግጅቱ የደረሰበት ደረጃ ማየት እና ተጨማሪ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ ታሳቢ ባደረገው ውይይት ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና ብሩክ ታዬን(ዶ/ር) ጨምሮ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top