Mols.gov.et

በልምድ ለተገኘ ሙያ እውቅና መሰጠቱ ምርታማነትን ከመጨመር ባለፈ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች እንዳሉት ተገለፀ

September 30, 2024
በልምድ ለተገኘ ሙያ እውቅና መሰጠቱ ምርታማነትን ከመጨመር ባለፈ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች እንዳሉት ተገለፀ በልምድ የተገኘ ሙያን በምዘና በማረጋገጥ እውቅ መስጠት የሚያስችል መምሪያ ትላንት በአዲስ አበባ ይፋ ተደርጓል፡፡ ይህን ተከትሎ የዘርፉ አስፈፃሚ፣ ባለድርሻ እና አጋር አካላት እንዲሁም የተለያዩ ድርጅት ተወካዮች ውይይት አካሂደዋል፡፡ በዚህም በልምድ ለተገኘ ሙያ እውቅና መሰጠቱ ምርታማነትን ከመጨመር ባለፈ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች እንዳሉት ነው የተገለጸው፡፡ በርካታ ዜጎች በመደበኛው የትምህርትና ስልጠና ስርዓት ሳያልፉ የተለያዩ ሙያዎች ባለቤት ሆነው በሥራ ገበያውና በኢኮኖሚው ውስጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንዳሉ ተመላክቷል፡፡ ይህ እውቅና እንዲያገኝ መደረጉ ባለሙያዎቹ እያደረጉ ያለውን አስተዋጽኦ የሚያልቅ እንደሆነም ነው በመድረኩ ላይ የተነሳው፡፡ ስርዓቱ ባለሙያዎቹ ምርትና ምርታማነታቸው እንዲጨምር ከማድረግ ባሻገር የክህሎት ክፍተታቸው ተለይቶ እንዲሞላ፣ የሥራ ዕድልና ተጠቃሚነታቸው እንዲሰፋ፣ ሀገር በቀል ሙያዎች እንዲጎለብቱ እንዲሁም በልምድ ሙያ ያላቸውን ዜጎች ብቃታቸውን በማረጋገጥና ወደ መደበኛው ስርዓት በማስገባት የሥራ ገበያው ላይ ብቁና በቂ የሰለጠነ የሰው ሃይል እንዲኖር የሚያደርግ እንደሆንም ነው የተገለፀው፡፡ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ውይይቱን ሲያጠቃልሉ እንደገለጹት የፕሮግራሙ ይፋ መሆን በሀገራችን በመደበኛና በአጫጭር ስልጠና በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሲሰጥ ከቆየው ስልጠና በተጨማሪ ዜጎችን የክህሎት ባለቤት ለማድረግ የሚያስችል ዋንኛ አማራጭ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top