Mols.gov.et

ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ለሀገር ምርታማነት ዕድገት

March 12, 2026
ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ለሀገር ምርታማነት ዕድገት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰላማዊ የሥራ አካባቢን በመፍጠር ምርታማነትን በማሳደግ እንዲሁም በአሠሪ፣ በሠራተኛና በመንግሥት መካከል የሚደረገውን የሶስትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገበ ይገኛል። በሚኒስቴሩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የሶስትዮሽ ግንኙነት ማስተባበሪያ ዴስክ ኃላፊ አቶ እንዳልክ ተክለኃዋርያት እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል በዘርፉ ይስተዋል የነበረው አሉታዊ ግንኙነት በአዲስ መልክ እንዲቀየር ተደርጓል። “ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ለሀገር ምርታማነት ዕድገት ወሳኝ መሠረት ነው” ያሉት አቶ እንዳልክ፣ ሚኒስቴሩ ወሳኝና አማካሪ ቦርዶችን በሁሉም ክልሎችና የኢንዱስትሪ መንደሮች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል። ባለፉት ስድስት ወራት ሚኒስቴሩ የቦርዶችን አቅም ለመገንባትና አሠራራቸውን ለማዘመን በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። በዚህም መሰረት ለወሳኝ ቦርዶች የቀረቡ የወል የሥራ ክርክሮች በውይይትና በስምምነት እንዲቋጩ ተደርጓል። ይህም ሠራተኞች የሥራ ዋስትናቸው ሳይቋረጥ እንዲቀጥሉ፣ ድርጅቶችም ያለምንም መስተጓጎል ወደ ምርታማነት እንዲመለሱ አስችሏል ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top