X
60%

Mols.gov.et

ማህበራትን በማጠናከርና የሥራ ቦታን ምቹ በማድረግ በአሠሪና ሠራተኛ መካከል ሠላማዊ ግንኙነት እንዲኖረ፣ እና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ

August 28, 2023
የኢንዱስትሪ ሠላም ለማስጠበቅና የተደራጁ የአሠሪና ሠራተኛ ማህበራትን በመከታተልና በመደገፍ ማህበራቱ የተደራጁለትን ዓላማ እንዲያሳኩ የሚያግዝ ማጠናከሪያ ድጋፍ መምሪያ ተዘጋጅቶ ለተግባራዊነት ቀርቧል። ማህበራቱ እንዲጠናከሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትብብርና ጥምረት መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ ግንኙነት የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተካልኝ አያሌው ማህበራትን በማጠናከርና የሥራ ቦታቸው ምቹ በማድረግ በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የሠመረ ሠላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት እንዲኖረ፣ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ማድረግ ይቻላል ብለዋል። ጠንካራ የሠራተኞች ማህበራት አሠሪና ሠራተኞች በጋራ ጥቅሞቻቸው ላይ በመመካከርና በመደራደር ስምምነት ላይ ለመድረስ ጉልህ አስተዋፅዖ አላቸው ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው ነባሩን የአሠሪና ሠራተኛ አስተሳሰብ መለወጥ አንዱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እሳቤ መሆኑን አስረድተዋል። የተዘጋጁት ሰነዶች እየተካሄደ ባለው ውይይት በሚገኘው ግብዓት መሰረት ተስተካክለው ለእያንዳንዱ ክልል መድረስ እንዳለበትም ጠቁመው በቀጣይም ከማህበራቱ ጋር ውይይቶች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል።
en_US