Mols.gov.et

ለ43,500 ሰዎች የሥራ እድል!…

August 1, 2024
ለ43,500 ሰዎች የሥራ እድል! የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች ውስጥ የግብርና ናሙና ቆጠራ ያከናውናል፡፡ስለሆነም በቀበሌው የሚሰማሩ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የሚያሟሉ መረጃ ሰብሳቢዎችን አወዳድሮ በኮንትራት መቅጠር ይፈልጋል። በዚህም መሰረት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት(ሌበር ማርኬት ፖርታል- E-LMIS) በመጠቀም ከመላ የሀገሪቱ ክፍሎች 43,500 ሰራተኛ ይፈለጋል። ስለሆነም በዚህ የሥራ እድል ተጠቃሚ ለመሆን lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ አንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር ይዛችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። የሥራ መደቡ መጠሪያ፡- የስታቲስቲክስ መረጃ ሰብሳቢ ብዛት፡- 43,500 ፆታ ፡- ጾታ አይለይም የሥራ መደቡ ዓላማ ፡-ጥራቱን የጠበቀ የገጠር/ከተማ የቤተሰብ/ባለይዞታ የግብርና መረጃ መሰብሰብ እና ወደ ሰርቨር መላክ
en_USEN
Scroll to Top