ለጀርመን የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት ምላሽ በመስጠት እና ሀገሪቱ አሁን ለደረሰችበት ኢኮኖሚያዊ ስኬት ጉልህ አስተዋፅዖ እንዳለው የሚነገርለት የፌደራል የሙያ ትምህርት እና ስልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር እና የምርምር ሃላፊ ከሆኑት ፕሮፌሰር ሚካኤል ሽዋርትዝ እና የኢንስቲትዩቱ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል፡፡
በውይይቱ በሀገሪቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናው ዘርፍ የምርምርና የልህቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ተመልክተናል። ከዚህ ባለፈ የጀርመን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስርዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ በስኬታማነት ከሚጠቀሱት መካከል ግንባር ቀደሙ እንዲሆን ማስቻሉንና በዘርፉ ያካበቱትን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠውልናል።
በጀርመን የፌደራል የሙያ ትምህርት እና ስልጠና ኢንስቲትዩት (bibb) ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስርዓት ውስጥ ያካበታችሁትን ልምድና ተሞክሮ ለማካፈል ላሳያችሁን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።