ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚሰጥ “ለመንገዴ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ
August 22, 2025

ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚሰጥ “ለመንገዴ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤት ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሐመድ በይፋ ማድረጊያ መርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ መተግበሪያ በራስ አቅም በልጽጎ ወደ ሥራ የገባ መሆኑን ገልፀው ይህም በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
መተግበሪያው በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎች ከቅድመ ጉዞ በፊት ማድረግ ስለሚኖርባቸው ቅድመ ዝግጅቶች፣ መብትና ግዴታዎቻቸውን ጨምሮ የተለያዩ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት እንዲያገኙ እንደሚያግዛቸውም ጠቁመዋል፡፡
ከመረጃዎቹ ባሻገርም ምንም አይነት ቅሬታም ሆነ ችግር በሚገጥማቸው ወቅት ለሚመለከተው አካል በቀላሉ ማሳወቅ እንዲቸሉ ዕድል የሚፈጥር መሆኑነም አመላክተዋል፡፡
መተግበሪያው የዜጎችን በሥራ ስምሪቱ የዜጎችን መብት፣ ደህንትና ተጠቃሚነትን ለማላቅ የሚኖረው አስተዋጾ ከፍተኛ መሆኑ የገለጹ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ “ኢትዮጵያ እየተከተለችው ያለውን የዲጂታል ስነ-ምህዳር ግንባታ አንዱ አካል ነው” እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪቱን ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል።
የዓለም የሥራ ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኩምቡላ ዳባ በበኩላቸው፤ መተግበሪያው መልከ ብዙ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸው መሰል ሥራዎችን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ይሰራል ብለዋል።
መተግበሪያውን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከዓለም የሥራ ድርጅት ጋር በመተባባር የተዘጋጀ ሲሆን መተግበሪያው በአማርኛ፣ በአረብኛና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች በቴሌብር ማግኘት እንደሚቻል በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል፡፡






