Mols.gov.et

ፖሊሲው በሀገራችን ኢንተርፕረነርሺፕ የዜጎች የማሰቢያ መንገድ ለማድረግ ትልቅ መሰረት የሚጥል ነው ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

August 27, 2025
ፖሊሲው በሀገራችን ኢንተርፕረነርሺፕ የዜጎች የማሰቢያ መንገድ ለማድረግ ትልቅ መሰረት የሚጥል ነው ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የመጀመሪያው የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነድ ላይ የሚመክር የግብዓት ማሰባሰቢያ የምክክር መድረክ ተካሂደ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በኢትዮጵያ ኢንተርፕረነር የሆነ መንግስት እየተገነባ መሆኑን ገልጸው እየተዘጋጀ የሚገኘው ፖሊሲ ኢንተርፕረነርሺፕ የማህበረሰቡ የማሰቢያ መንገድ እንዲሆን ለማድረግ መሰረት የሚጥል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ መንግስት በሀገራችን የኢንተርፕረነርሺፕ ስነምህዳር ለመገንባት ካለው ቁርጠኝነት የተነሳም አስተሳሰቡን የሚያሰርጽ በግብዓት እና በሰው ኃይል የተደራጀ የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ተቋም አቋቁሞ ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ባለፉት ሦስት ዓመታት ኢንተርፕረነርያል የሆኑ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መገንባት እንደተቻለ አመላክተዋል። ስነ ምህዳሩን ምቹ ለማድረግ በተደረው ጥረትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳድረው ማሸነፍ የቻሉ ባለሙያዎችንና ፕሮጀክቶች እውን ከማድረግ ጀምሮ በፊት ዝግ የነበሩ አሰራሮችን በመከፋፈት ሰፋፊ ስራዎች እንዲሰሩ እድል መፍጠሩንም አብራርተዋል፡፡ ፖሊሲና ስትራቴጂው ድንበር እና ዘመን የሚሻገሩ ስራዎችን መስራት እንዲያስችል በተቻለ መጠን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ግብዓት ታክሎበት ተግባራዊ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top