Mols.gov.et

“ፕሮግራሙ ወጣቶች በተጨባጭ የሥራ ልምድ ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ክህሎትን የሚያላብሳቸው ነው፡፡” …

February 17, 2024
“ፕሮግራሙ ወጣቶች በተጨባጭ የሥራ ልምድ ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ክህሎትን የሚያላብሳቸው ነው፡፡” ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የመጀመሪያው ዙር ማጠቃለያ እና የሁለተኛ ዙር ምዕራፍ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በድሬደዋ ከተማ ተከናውኗል። በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለፁት፤ መንግስት የሥራ አጥነት ምጣኔን ለመቀነስ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርም የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራው ክህሎት መር እንዲሆን አቅጣጫ አስቀምጦ በዘርፉ ሰፊ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ሚኒስቴር መ/ቤቱ በመደበኛ የሥራ ዕድል ፈጠራ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጓዳኝ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር “ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም” ተግባራዊ በማድረግ ትምህርታቸውን በተለያየ ምክንያት ያቋረጡ ወጣቶችን ተጠቃሚ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ይህ ፕሮግራም ወጣቶች በሥራ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን አቅም ከመገንባት አንፃር በርካታ ልምድና ተሞክሮዎች የተገኘበት ነው፡፡ ፕሮግራሙ ወጣቶች በተጨባጭ የሥራ ልምድ ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ክህሎትን የሚያላብሳቸው ነው ብለዋል። ለፕሮግራሙ ስኬት አበርክቶ ለነበራቸው የዘርፉ አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች ምስጋና ያቀረቡት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በፕሮግራሙ አንደኛ ዙር ትግበራ የተገኙ ተሞክሮዎችን ቀምሮ በሁለተኛው ዙር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መረባረብ እንደሚገባቸው አሳስበዋል። የድሬዳዋ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁዋር በበኩላቸው፣ መርሃ ግብሩን በጋራ እውን ላደረጉት ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ለዓለም ባንክ ምስጋና አቅርበው በከተማ የጀመረው መርሃ ግብር ወደ ገጠር አካባቢም እንዲሰፋ ጠይቀዋል። የድረዳዋ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፤ ብቃት የሥራ ላይ ልምምድ ከተሳተፉት ወጣቶች መካከል 96 በመቶ የሚሆኑትን ቋሚ የስራ ዕድል ባለቤት ማድረግ ተችሏሏ። ከዚህ ባለፈም ለሁለተኛ ዙር ትግበራ መሰረት የጣለ፣ የመንግስት እና የግሉን ዘርፍ አጋርነት ያጎለበተ እና የሥራ ላይ ልምምድ ባህል እንዲዳብር ያስቻለ ስኬታማ ፕሮግራም ነው ብለዋል።
en_USEN
Scroll to Top