Mols.gov.et

ፍልሰት ጋር ያሉ ተያያዥ ችግሮችን ከመሰረቱ ለመቅረፍ ለችግሩ ምንጭ የሆኑ ነገሮች ላይ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

August 30, 2023
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) የኢትዮጵያ ተወካይ አቢባቱ ዋኔ ጋር ተወያይተዋል። ክብርት ሚኒስትር በውይይቱ ላይ እንደገለፁት፣ ፍልሰት ጋር ያሉ ተያያዥ ችግሮችን ከመሰረቱ ለመቅረፍ ለችግሩ ምንጭ የሆኑ ነገሮች ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል። ስለሆነም የክህሎት ልማቱን ማፋጠን፣ ቀጠናዊና አህጉራዊ ትስስርን ማጠናከር፣ ምርጥ አሰራርና ተሞክሮዎችን መለዋወጥ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት እና እሴት አካይ ድጋፎችን ማስፋት ይገባል ብለዋል፡፡ የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) የኢትዮጵያ ተወካይ አቢባቱ ዋኔ በበኩላቸው ፍልሰትና ነፃ የጉልበት ዝውውር ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጋር የሚሰሩትን ሥራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
en_USEN
Scroll to Top