Mols.gov.et

ፀጋዎቻችንን አልምቶ ከመጠቀም ባለፈ…

May 13, 2024
ፀጋዎቻችንን አልምቶ ከመጠቀም ባለፈ… ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መሥተዳድር ክቡር አቶ አሻድሊ ሀሰን ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡ በውይይቱ ላይ በክልሉ ያለውን ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት በማልማት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት እንዲሁም በሥራ ዕድል ፈጠራና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚሹ ሥራዎችን መመልከት ተችሏል፡፡ በዚህም የእሴት ሰንሰለትን መሰረት ያደረገው ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫችን እሴት አካይ ድጋፍና ክትትል እንደሚያስፈልገው እና ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ወደ ህብረተሰቡ ማድረስ እንደሚያስፈልግ የጋራ ሀሳብ ተይዟል። ከውይይቱ ባለፈ በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍ እውቅና ባገኘው የብየዳ ማዕከል በልዩ የክረምት ወራት የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ እና የፈጠራ ሀሳቦች ማሻሻያ መርሃ ግብር እየተሰሩ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን በጋራ ተጉብኝተዋል፡፡ በዚህም በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ፀጋዎችን በአግባቡ አልምቶ ከመጠቀም ባለፈ ተኪ ምርቶች ላይ ሀገራዊ አቅም ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት የሚያግዙ ጥረቶች እና ውጤቶች አበረታች መሆናቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናግረዋል ።
en_USEN
Scroll to Top