Mols.gov.et

ፀጋዎቻችንን አልምቶ ለመጠቀም…

January 7, 2024
ፀጋዎቻችንን አልምቶ ለመጠቀም… ተቋማችን ፍላጎት፣ ብቃትና ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶችን በማሰባሰብ ቴክኖሎጂ እንዲሰሩና የፈጠራ ሀሳባቸውን እንዲያዳብሩ በሚያስችለው መርሃግብር የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ ለማዋል ከማዕድን ሚንስትር ክቡር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደናል። በውይይታችን የማዕድን ዘርፉ ጋር የተያያዙና የተጀመሩ የክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና የሙያ ደህንነትና ጤንነት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚቻልበት ሁኔታን ተመልክተናል። በክረምት ወራት የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያና የፈጠራ ሀሳቦች ማሻሻያ መርሃ ግብር የተሰሩ በማዕድን ልማት፣ በግብርና፣ በግንባታ ፣ በጤና እና በሌሎችም መስኮች የሚያገለግሉ ቴክኖሎጂዎችን ጎብኝተናል፡፡ የማዕድን ሚንስትር ክቡር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ ፀጋዎቻችንን አልምቶ ለመጠቀም የሚያስችሉና በወጣቶቻች የተሰሩ ቴክናሎጂዎችን ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍና ከዚህ ቀደም የተጀመሩ ሥራዎችን አልቆ ለማስቀጠል ላሳዩን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ፡፡
en_USEN
Scroll to Top