Mols.gov.et

ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስርዓት፤ ለላቀ ውጤት!

November 21, 2024
ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስርዓት፤ ለላቀ ውጤት! የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከክህሎት ልማት፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ እና ከአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ አኳያ የተሰጡትን ግዙፍ ተልዕኮዎችን ለማሳካት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ “አመተ ማፅናት” በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች ጋር የዕቅድ አፈፃፀሙን በተናጥል ገምግሟል፡፡ በክህሎት ልማት ዘርፉ የሥራ ገበያውና የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሚፈልገውን ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት የሚያስችል ስርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም እስካሁን ከመደበኛው ባሻገር በገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠና በርካታ ዜጎችን የሙያ ባለቤትና ምርታማ እንዲሆኑ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት አበረታች መሆኑ ተገምግሟል፡፡ የየአካባቢውን ችግር የሚፈቱና የውጭ ምርትን የሚተኩ ቴክኖሎጂዎችን የማልማት፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የስልጠና ጥራታቸውን በሚያረጋግጥ መልኩ የኢኮኖሚ አቅማቸውን እንዲያሳድጉና የየአካባቢያቸውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ እንዲያደርጉ እንዲሁም በተለያዩ አግባቦች ሙያ ያላቸው ዜጎች ብቃታቸውን በምዘና በማረጋገጥ ወደ ሥራ ገበያው ተቀላቅለው ምርትና ምርታማነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ተጨማሪ አቅም እንዲሆኑ የማድረጉ ጥረት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አሳይቷል፡፡ በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በልጽጎ በየደረጃው ሥራ ላይ እንዲውልና በመረጃ እንዲዳብር እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎቻችን በቴክኖሎጂ የታገዙ እንዲሆኑ ከማድረጉም ባሻገር በትምህርትና ሥልጠና እና የሥራ ገበያ ላይ የሚሰጡ የፖሊሲ ውሳኔዎች በጠናካራና አስተማማኝ መረጃ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ መሰረት መጣል ያስቻለ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ክህሎት መር በሆነው የሥራ እድል ፈጠራ አቅጣጫችን ከኢኮኖሚው እድገት ጋር የሚተሳሰሩና እሴት ሰንሰለትን መሰረት ያደረጉ ጥራት ያላቸው የሥራ ዕድሎችን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለመፍጠር እየተደረገ ያለው ርብርብና እያስገኛ ያለው ውጤትም ተጨባጭ ነገር ግን በእግጁ ማላቅን የሚጠይቅ እንደሆነ ለማየት ተችሏል፡፡ አዳዲስ የሥራ ፈጠራ ሀሳቦችን በኢንተርፕሪነርሺፕ ለመኮትኮትና ለማፍራት፣ ፈጠራን ማዕከል ያደረጉና እሴት አካይ የሆኑ መንግስታዊ ድጋፎች እንዲሁም ቴክኖሎጂ መር የገበያ መሰረተ ልማቶችን ለማቅረብ የተጀመሩ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት እያሳዩ መሆናቸውም ታይቷል፡፡ በቀጣይ ቤሰተብንና ማህበረሰብን የምርታማነት ማዕከል በማድግ አንድ አካባቢ የራሱ መለያ የሆነ አንድ ምርት እንዲኖረው ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም አቅጣጫ ተቀምተጧል፡፡ ከክርክር ይልቅ ምክክርን በማስቀደም ምርታማነትን ማዕከል ያደረገ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ለመፍጠር፣ የሙያ ደህንነትና ጤንነነትን ለማረጋገጥ፣ ዘመናዊ የሥራ ሁኔታ ቁጥጥርን ለማስፈን፣ የአሠሪና ሠራተኛ የመደራጀት ምጣኔን ለማሳደግ እንዲሁም የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የዜጎችን ክብር፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ያረጋገጥ እንዲሆን ለማድረግ የተጀመረው ጥረትም የሚያበረታታ ውጤቶች የተገኙበት እንደሆነ ተገምግሟል፡፡ ከህዳር 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ የአመራር የድጋፍና ክትትል ቡድን ተዋቅሮ የሥራ ስምሪት አድርጓል፡፡ በዚህም በ2016 በጀት ዓመት የተደረገውን ተመሳሳይ የድጋፍና ክትትል ስምሪት ውጤታማነት በማየት በዘርፉ የአቅጣጫ ግልፅነትና የጎንዮሽና የተዋረድ ቅንጅታዊ አሰራር እንዲጎለበት ለማድረግ እንደሚያግዝ ይታመናል፡፡ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማው የታዩ ክፍተቶችን በማረም በሦስቱም ዘርፎች የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ያለመው ይህ የክትትልና ድጋፍ ቡድን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ ነው፡፡
en_USEN
Scroll to Top