ጠንካራ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ለወጣቶች ተሳተፊነት እና ተጠቃሚነት
5ኛው የምስራቅ አፍሪካ የሚኒስትሮች የፍልሰት ጉዳዮች ፎረም የቴክኒክ ቡድን በዛሬ ውሎው በቀጠናው ሀገራት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት እና የወጣቱ ተሳትፎ የተመለከቱ ጉዳዮችን ተመልክቷል፡፡
በቀጠናው ሀገራት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ላይ የወጣቱ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ፤ ከሩዋንዳ፣ ከኢትዮጵያ ፣ ከቡሩንዲ እና ከታንዛኒያ የተወከሉ ወጣቶች በፓናሊስትነት የተሳተፉበት የፓናል ውይይትም ተካሂዷል፡፡
“የመደበኛ ፍልሰት ትሩፋቶች ለወጣቶች የሥራ ዕድል፣ ለክህሎት ልማት እና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ፎረም ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት አኳያ በቀጠናው ሀገራት ያሉ ልምዶች እና ተሞክሮችንም በጥልቀት ተዳሰዋል፡፡
የዓለም ከፍተኛ ስጋት የሆነው የአየር ንብረት ለውጥ ለመቆጣጠር፣ ድርቅ እና እረሃብ የመሳሰሉትን ችግሮች በዘላቂነት ለመቋቋም እና የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማይት ሥራ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም ተገልጿል፡፡