Mols.gov.et

ጊዜው የሚጠይቀው አርበኝነት ድህነትን ድል መንሳትና የዜጎቻችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው፡

December 26, 2023
“ጊዜው የሚጠይቀው አርበኝነት ድህነትን ድል መንሳትና የዜጎቻችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው፡፡” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በዘርፉ የሪፎርም ሥራዎች ላይ ያተኮረ የሥልጠናና የምክክር መድረክ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎች እና ከፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች ጋር እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በመድረኩ የዘርፉን አዲስ እሳቤና በሚኒስቴር መ/ቤቱ እየተከናወኑ የሚገኙ የሪፎርም ሥራዎችን አስመልክተው ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለፃ አድርገዋል፡፡ ክብርት ሚኒስትር በሰጡት ማብራሪያ ዘርፉ ዜጎችን ከድህነት የሚያወጡ ሰው ተኮር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸው ጊዜው የሚጠይቀው አርበኝነትም ድህነትን ድል መንሳትና የዜጎቻችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡ ክህሎትን የማሰቢ መንገድ አድርጎ መውሰድ፣ በቴክኒክና ሙያ ዘርፉ የሚሰጡ ሥልጠናዎች ገበያ መር ማድረግ ፣ ሰልጣኞች የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ ፈጥረው እንዲወጡ ማስቻል ፣ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰጡ ሥልጠናዎች በአንተርፕረነርሺ እሳቤ መቃኘት እና ተቋማቱ እራሳቸውን የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር የክህሎት ዘርፍ ዋነኛ የሪፎርም አጀንዳዎች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ የሥራ ዕድል የሚፈጠርላቸው ዜጎች መሰረታዊ የሚባሉ ክህሎቶች የታጠቁ እንዲሆኑ መሥራት፣ ከፍተኛ የማደግ አለኝታ ያላቸው ኢንተርፕራይዞች በልዩ ሁኔታ መደገፍ እና የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ንግድ ማስፋፋት ከሥራ ዕድል ፈጠራ አኳያ ያሉ አንኳር እሳቤዎች ናቸው ብለዋል፡፡ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ከዚህ በፊት የነበረውን ትርክት ምርታማነትን ማዕከል ባደረገ የግንኙነት አግባብ መቀየር እና አዲስ የኢንዱስትሪ ባህል መገንባት ላይ ትኩረት ያደረገ አዲስ እሳቤን እንደሚከተልም ገልፀዋል፡፡ የዘርፉ ተልዕኮ የትናንትን ዕዳ፣ የዛሬን ዕድልና የነገን ተስፋ መሰረት ያደረገ ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት አገርና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ተልዕኮን በፍጥነትን ፣ በብዛትንና በጥራት መፈፀም ከእያንዳንዱ የዘርፉ አስፈፃሚ አካል የሚጠበቅ ወሳኝ ኃላፊነት መሆኑን በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top