Mols.gov.et

ጉባኤው ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ እና አይቲ ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም ለተቀሪው አለም ለማስተዋወቅ ትልቅ አቅም ይኖረዋል፡፡ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ደኤታ

October 12, 2023
የተለያዩ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች፣ ቴክኖሎጂስቶች፣ ኢንቨስተሮች እና በድጅታል ኢኮኖሚ የተሰማሩ አካላት የሚሳተፉበት የእንቆጳ ጉባኤ (Enkopa summit) በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሎራንዶ እና አሶሼትስ(Laurende associates) እና ከፍሎውለስ ኢቨንትና ጋር በቅንጅት ያዘጋጁት እንቆጳ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሚኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በጉባኤው መክፈቻ እንደገለጹት፣ ጉባኤው ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ እና አይቲ ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም ለተቀሪው አለም ለማስተዋወቅ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ፡፡ ድጅታል ኢኮኖሚ፣ ቴክኖሎጂ እና አይቲ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ዘርፎች መሆናቸውን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራችንም በአይቲ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም አውጥቶ ለመጠቀም እንቆጳ ጉባኤ መዘጋጀት መጀመሩንም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ጉባኤው ሀሳብ ያላቸው ጀማሪ ቢዝነሶች ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በዘርፉ ከተሰማሩ አካላት ጋር የሚተዋወቁበት፣ ልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት እና ምርቶቻቸውን የሚያስተሳስሩበት እድል እንደሚፈጥርላቸው ገልጸዋል፡፡ በጉባኤው በሀገራችን የሚገኙ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች የሥራ እንቅስቃሴያቸውን የሚያሳይ ኤግዚቢሽን የተዘጋጀ ሲሆን በሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮሩ የተለያዩ የፓናል ውይይቶች እየተካሄዱ ይገኛል፡፡
Scroll to Top