Mols.gov.et

ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ……

October 25, 2025
መንግስት የነገውን አለም እጣ ፈንታ የሚወስነውን ድጅታል ኢትጵያ እውን ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ ክቡር ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ የቢዝነስ ፕሮሰስ አውቶሶርሲንግ ኢኮሲስተም ኢንሼቲፍ ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር) ጨምሮ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት መልዕክት ያስተላለፉት ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፣ መንግስት የነገውን አለም እጣ ፋንታ የሚወስነውን ድጅታል ኢትጵያ እውን ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ በዚህም ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ የተለየውን የአይሲቲ መሰረተ ልማት ማስፋፋትና የቴሌኮም ዘርፍ ለገበያ ክፍት ማድረግን ጨምሮ የመንግስት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ በድጅታል አማራጭ በማቅረብ ድጅታል 2030 እውን ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የድጅታል ቴክኖሎጂ በመስፋፋቱ ምክንያት ለወጣቶች ዘርፈ ብዙ በረከቶች እየመጡ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው ከነዚህ በረከቶች መካከል ወጣቶች ባሉበት ቦታ ሆነው በየትኛውም አለም ክፍል የሚገኝን ሥራ በርቀት እንዲሰሩ በር ተከፍቷል ብለዋል፡፡ በዚህ የእርቀት ስራ ባለፉት ዓመታት በአስርሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ተሰማርተው ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ከማግኘት ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደቻሉ አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ በቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ ስራ ተደራጅተው የተሰማሩ ተቋማት ከትላልቅ የአለማችን ኩባንያዎችና ድርጅቶች የተወሰነውን የሥራ ሂደት ሥራ ወስደው በመተግበር ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በዚህ ዘርፍ ሀገራችን ተወዳዳሪ ለማድረግ የኢትየዮጵያ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ ማህበር ተቋቁሞ ዉጤታማ ተግባራት በማከናወን እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡ ሸገር ከተማም በዛሬው ዕለት የነገውን የሥራ ዓለም የሚወስነውንና ለበርካታ ወጣቶች ጥራት ያለው የሥራ እድል መፍጠር የሚያስችለውን የቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ ሥራ በይፋ መቀላቀሉን ገልጸዋል፡፡ ወጣቶች በመሰል ድጅታል ሥራዎች ተጠቃሚ ለመሆን ድጅታል ክህሎት መታጠቅ አማራጭ የሌለው በመሆኑ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ(ዶ/ር) ይፋ የተደረገውን የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠናን ጨምሮ በሌሎችም የድጅታል ክህሎቶች እራሳቸውን ብቁ አድርገው ለሥራ ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top