የጤናውን ዘርፍ አቅም ማሳደግ ነገ ማየት የምንፈልጋትን የበለፀገች ኢትዮጵያ ጤናማ መንገድ የመቅረፅ አካል ነው::
April 27, 2024
የጤናውን ዘርፍ አቅም ማሳደግ ነገ ማየት የምንፈልጋትን የበለፀገች ኢትዮጵያ ጤናማ መንገድ የመቅረፅ አካል ነው::
በጤናው ዘርፍ ሥራ ስራ ስምሪትንና የክህሎት አቅም ግንባታን ለማሳደግ በትብብር ለመስራት ስልቶችን ለመንደፍ ከጤና ሚንስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር ውጤታማ ምክክር ሰለማድረጋቸው ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናግረዋል፡፡
በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚገኙ የጤና ዘርፍ የሥራ እድል ፍላጎት በተገቢው ክህሎትና አስተሳሰብ በተገነባ ብቁ የጤና ባለሙያዎች አቅርቦት ለማሟላት አቅማችንን በትብብር የማሳደግ ስልቶች ላይ በትኩረት መወያየታቸውንም ገልጸዋል፡፡
በጤናው ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም ለሥራ ገበያው በማቅረብ ዜጎችንና ሀገርን ለመጠቀም እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳለጥ የጤና ባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ የትብብሩ ቁልፍ ተግባር ይሆናል::
ሙያዊ ክህሎትን ከማሳደግ ባሻገር የውጭ ሀገር ሥራ ዕድሎችን በተገቢው በማሰስ የሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎቻችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለጤና አጠባበቅ ምህዳሩ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ የሚያግዙ መንገዶችን መፍጠር በትኩረት የምንሰራበት ይሆናል።
አክለውም ወ/ሮ ሙፈሪሃት ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና አጠባበቅ ዘርፉን ለማጠናከር እና ለጤና ሰራዊታችን በሀገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሥራ ዕድልን ለማስፋት በትብብር ለመስራት ያሳዩትን ቁርጠኝነት እጅጉን አደንቃለሁ! ለነበረን ጥልቅ እሩቅ አላሚና ችግር ፈች መንገዶችን ጠቋሚ ውይይት ክልብ አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡